እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ጋብቻናሙና
ክርስቶስን መምሰል
የዛሬው ንባባችን የሚመራን ወደ መጀመሪያው ወደ አዳምና ሙሽሪት ወደ ሆነችው ወደ ሔዋን ግንኙነት ሁነት ነው፡፡ እግዚአብሔር በታሪክ የመጀመሪያውን ቀዶ ጥገና በአዳም ላይ አድርጓል፡፡ ከባድ የሆነን እንቅልፍ በአዳም ላይ እንደ ማደንዘዣ ሰጥቶት ደረቱን ከፍቶ የጎድን አጥንቱን አስወግዶ ሴትን ሰራ፡፡ አዳም በሂደቱ ላይ ምንም ዓይነት ንቁ ተሳትፎ እንኳን አላደረገም፤ እግዚአብሔር ነው የምትመች፣ የምትጣጣም አቻ አጋር ያዘጋጀለት፡፡ ለሞት ከቀረበ ጥልቅ እንቅልፍ ሲነቃ በግጥም፡- ሙሽሪትን በደስታ ሊያገኛት፤ የራሱን አጥንት እና ከስጋው የሆነ ስጋ ሲል ምላሽ ሰጠ፡፡
ሔዋን የተፈጠረችበት መንገድ እጅግ ታላቅነው፡፡ አዳም እጅግ ውድ የሆነውን የራሱን የአካል ክፍሉን አጥቷል ከዚያ ከጎደለው የአካል ክፍሉ ግን ሙሽሪት ትመጣለች፡፡ያጣው ነገር የማይቆጠር በረከት ይዞለት ወደ ውብ ስጦታ መራው፡፡ እኚህ በኤደን ገነት የነበሩት ዝግጅቶች ኢየሱስ ሙሽሪት የሆነችውን ቤተ-ክርስቲያንን እንዴት እንደተቀበላት ያንፀባርቃል፡፡የአዳምን የጎድን አጥንት ለማስወገድ እግዚአብሔር የአዳምን ጎን እንደከፈተ የኢየሱስም ጎን በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ ተከፍቷል፡፡ ኢየሱስ በተለየ ሁኔታ የጎድን አጥንቱን አይደለም ያጣው እኛን ለማትረፍ ህይወቱን እንጂ፡፡
በጋብቻ ግነኙነት ውስጥ አዳምና ኢየሱስ ሁለቱም ራስን መስዋዕት የማድረግን ተመሳሳይነት ያሳያሉ፡፡ ይህ ላገቡትም ሆነ ለማግባት ዕቅድ ላላቸው አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡ አስደናቂውን የጋብቻ ስጦታ ምንም ዋጋ ሳትከፍልበት ለመቀበል አትጠብቅ፡፡ የቅርብ፣ ዘላቂና አንድ የሆነ ጋብቻን ለማግኘት በጣም የምትወደውን ማንነት መስዋዕት ማድረግ ይኖርብሃል፡፡ ራስን መስዋዕት ማድረግ ማለት መጀመሪያ ስታገባ የምትፈፅመው የአንድ ጊዜ ክስተት አይደለም፤ ይልቅ በማንኛውም ደስተኛ ጋብቻ ውስጥ ቋሚ ሊሆን የተገባው ነው፡፡ እንደ ባሎች፤ እንደ መሪነታችን ህይወታችንን ለሚስቶቻችን አሳልፈን ለመስጠት የፈጠንን መሆን አለብን፡፡
በአብዛኛው የአፍሪካ ክፍሎች ወንዶች የቤታቸው መሪ እንደሆኑ ይነገራል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ባል የቤተሰቡ ራስ ነው ይላል፤ ነገር ግን ይህ ማለት ሰውዬው ዝም ብሎ ተቀምጦ ቀንና ማታ እንዲያገለግሉት ይጠብቅ ማለት ግን አይደለም፡፡ ራስ መሆን ማለት አስቸጋሪ በሚባሉ የገንዘብ፣ የማህበራዊ፣ የስሜት፣ ግንኙነት ወይም ደግሞ በቤተሰብ ዕቅድ ሁኔታዎች ላይ የመጀመሪያ ሆኖ መምራት ማለት ነው፡፡
እንዲሁም ደግሞ የዛሬው የንባብ ክፍል ሰው (ወንድ) እናትና አባቱን የሚተወው ላይነጣጠል ከሚስቱ ጋር ሊገጥም መሆኑን ግልጽ ያደርግልናል፤ ከዚህ የተለየ ትርጉም ከሆነ እውነት አይደለም፡፡ በእናንተ ባህልና ማኅረሰብ ውስጥ እንደዚህ የማይጠበቅ ከሆነ ምናልባት ከዘመዶችህ ጋር ሁሉ ሳይቀር ድንበር ማበጀት ይጠበቅብህ ይሆናል፤ እንደሁም ለአንዳንድ አስቸጋሪ ንግግሮች ሁሉ መዘጋጀት ያስፈልግሃል፡፡
ጋብቻ ወንድና የሴትን አንድ የሚያደርግ ጥምረት፤ የህይወት ዘመን የእርስበርስ ታማኝነት ሲሆን ይህም ህይወቱን ለቤተ ክርስቲያን አሳልፎ የሰጠውንና እኛን ከእርሱ ጋር ለዘለዓለም አንድ ያደረገን የታላቁ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ እርሱ መቼም አይተወንም አይረሳንምም፡፡ እኛም በተለይ ያገባን ወንዶች እግዚአብሔር እኛን ምርጥ ስጦታ ለሆነችው ለሙሽሪት የበረከት ምንጭ እንዲያደርገን ይህንን ምሳሌነት ዋና ግባችን ማድረግ ያስፈልገናል፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ያገባህም/ሽም ሁን/ኚ ልታገባ/ቢ የምትፈልግ/ጊ ይህ የ3 ቀናት የንባብ ዕቅድ በህይወት/ሽ ዘመን ላለው የባልነት ወይም የሚስትነት መሰጠት የእግዚአብሔርን መልካም ዓላማ እንድታውቅ/ቂ ይረዳሃል/ሻል፡፡ የጥምረትን፣ መብዛት፣ የአዋጅን፣ የቅድስናንና የእርካታን ዓላማዎች በመፈለግ ኢየሱስ ለሙሽሪት ቤተ-ክርስቲያኑ ያለውን ፍቅር ማንፀባረቅን ተማር፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Kip' Chelashaw ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://christchurchke.org/