ወደ ቆላስይስ ሰዎችናሙና
በቆላስይስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ጥቂት መሪዎች ሐዋርያው ጳውሎስ ሁሉንም እውነት እንደነገራቸው ይጠራጠራሉ፡፡ የእግዚአብሔርን ሙላት ለመለማመድ ኢየሱስን ከማመን በተጨማሪ ሌሎች መንፈሳዊ ተግባራት ያስፈልጋሉ ብለው ማስተማር ጀምረዋል፡፡ የቆላስይስ ቤተ ክርስቲያን መስራች የሆነው ኤጳፍራ ጉዳዩ ግድ ቢለው ምክር ፍለጋ ወይኒ ወዳለው ጳውሎስ አቀና፡፡ እርሱም ለጳውሎስ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስላሉት መልካም ነገሮች ሁሉ ነግሮት ግን ደግሞ መሪዎቹ እያሰራጩት ያሉትን አስተምዕሮም ነገረው፡፡ ለቆላስይስ የተፃፈው ደብዳቤ የጳውሎስ ምላሽ ነው፡፡
ይሁን እንጂ በቆላስይስ ወደነበሩት ችግሮች ከመግባቱ በፊት ጳውሎስ እግዚአብሔር ስላደረገላቸው ነገር ቁልጭ አድርጎ ማሳየቱ ላይ አተኮረ፡፡ ጳውሎስ የቆላስይስ ቤተ ክርስቲያን ስላላቸው እምነት እግዚአብሔርን ያመሰግናል፡፡ እነርሱ ታማኞች፣ የሚወዱ፣ እና ኢየሱስ ስለመሞቱ፣ ስለመነሳቱ እና ስለዳግም ምፅዓቱ ያለውን የምስራች ተስፋ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ እግዚአብሔርን በአዲስ መንገድ ለማስደሰት ህይወታቸውን ከመሙላት ባለፈ ጳውሎስ የቆላስይስ ሰዎች በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ይሞሉ ዘንድ ይፀልይላቸዋል፡፡ ጳውሎስየእግዚአብሔርን ኃይል በመሞላት እግዚአብሔርን በሙላት የሚያስደስት ኑሮ እንደሚኖሩ እርግጠኛ ነው፡፡
የቆላስይስ ሰዎች ሙላትን በሌላ ስፍራ ከመሞከር ይልቅ ኢየሱስ ንጉሥ መሆኑን ማስታወስና ማመስገን ይገባቸዋል፡፡ ኢየሱስ የቆላስይስ ሰዎችን ከጨለማ መንግሥት በመታደግ እንዲሁም የእርሱ ትክክለኛው ዘላለማዊ የብርሃን መንግሥት ወራሾች እንደሆኑ ቃል ገብቶላቸዋል። ንጉስ ኢየሱስ ያለፈውን ጥፋታቸውን ይቅር ብሏቸዋል፡፡ እስካሁን የቆላስይስ ሰዎች ንጉሥ ኢየሱስ እያቀረበ ያለውን ነገር ሙሉ በሙሉ ለማጣጣም ምንም ያደረጉት ነገር የለም ስለዚህ አሁን መጀመር አያስፈልጋቸውምም፡፡
የቆላስይስ ሰዎች ሙሉ ለመሆን አማራጭ መንገዶችን ከመሞከር ይልቅ ኢየሱስ ሥልጣን ያለው ፈጣሪ መሆኑን ማስታወስ ይገባቸዋል፡፡ እርሱ ትክክለኛ ወራሽና የፍጥረታት ሁሉ ገዢ ነው፡፡ ኢየሱስ ሰማይንና ምድርን ፈጥሯል፡፡ ኢየሱስ የፖለቲካውም ሆነ የመንፈሳዊያን ኃይላት ፈጥሯል፤ እንዲሁም በሰማይና በምድር ያሉት ስልጣናት ሁሉ ለእርሱ ይሰራሉ፡፡ ኢየሱስ ህይወት ባለው ሁሉ ላይ ስልጣን አለው፤ እንዲሁም በሞት ላይም ስልጣን እንዳለው ትንሳኤው ያስረግጣል፡፡ ኢየሱስ የዓለማት ሁሉ የበላይ ሲሆን በደሙ እና በመስቀሉ አማካኝነት ደግሞ በአንድ ወቅት ርቆ የነበረውን ፍጥረቱን ወደ ፈጣሪነትኃይሉ ሙላት ቀላቅሏል፡፡
ከአንዳንዶቹ የይገባኛል ጥያቄ በተቃራኒ የእግዚአብሔር የሥልጣኑና የኃይሉ ሙላት በነጻነት ቀርቧል፡፡ የቆላስይስ ሰዎች ይህን አስቀድመው ያውቁታል ምክንያቱም የእግዚአብሔር ጠላቶች እንደነበሩም ያውቁታልና፡፡ ኢየሱስ ያለፈውን ክህደታቸውን ለመደምሰስ ሥልጣኑን እንደተጠቀመ ያውቃሉ እንዲሁም የእግዚአብሔር መንፈስ እግዚአብሔርን ለማስደሰት ሙሉ ኃይል እንደሰጣቸው ያውቃሉ፡፡ ይህ ሙላትን የሚሰጥ ብቸኛው ትምህርት ሲሆን የቆላስይስ ሰዎችም በዚሁ አስተምዕሮ ላይ ሲፀኑ ብቻ ነው እግዚአብሔርን ሊያስደስቱ የሚችሉት፡፡
ጳውሎስ እንደ ሐዋሪያነቱ የመጀመሪያ ስራው የኢየሱስን መልዕክት በሚገባ መግለፅ መሆኑን ይረዳል፤ በተለይም በሚያምኑቱ ውስጥ የሚኖረውን የእግዚአብሔር ሙላት የሆነውን የምስራቹን፡፡ የጳውሎስ ስራ አሁን በኢየሱስ በኩል ካገኘነው በላይ እግዚአብሔር ምንም የበለጠ የሚሰጠን ሌላ እንደሌለና ምንም ተጨማሪ እርምጃ እንደማያስፈልግ፣ ምንም የሞራል ድርጊቶችና ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች እንደማያስፈልጉ መግለፅ ነው፡፡
ጳውሎስ ሁለተኛው ሥራው የእግዚአብሔር ሙላት ያላቸውን ወደዚያም ማንነት እንዲበስሉና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝን ሕይወት እንዲመሩ ከማበረታታት ጋር የተዛመደ ነው ሲል ተናግሯል፡፡
ይሁን እንጂ ብስለት እኛ በምንጠብቀው መልኩ አይመጣም፡፡ በቆላስይስ ያሉ አስተማሪዎች እውነተኛ ብስለት እንደው በቀላሉ ኢየሱስን በመታመን ብቻ የሚመጣ ነው ከማለት ያልፋሉ፡፡ ነገር ግን የጳውሎስ የመጀመሪያው ምዕራፍ አጠቃላይ ነጥብ ዘላለማዊውን ኢየሱስን ቸል ብለን ወደ ብስለት ልንመጣ አንችልም የሚል ነው፡፡ በውስጥህ ካለው ከመንፈስ ቅዱስ አልፈህ መሄድ መቼም አትችልም፡፡ የኢየሱስ ተከታዮች ወንጌልን ወዲያ ብለው ወደ ብስለት ሊመጡ አይችሉም፡፡
እንደ ንጉስ ኢየሱስ ክፉ ስራችንን ሁሉ ይቅር ብሎን የብርሃንን መንግስት እንድንገዛ ሰጥቶናል፡፡ እንደ ፈጣሪ ኢየሱስ ፍጥረቱን የመፍጠር ሀይል ሙላት ወደሆነው ቀላቅሏል፡፡ በሞት ላይ እንዳለው ገዢነት ትንሳኤን ሰጥቷል፡፡ ስለዚህ የጳውሎስን ምክር ውሰዱ፡፡ ወንጌልን ቸል አትበሉ፡፡ ይልቅ የኢየሱስን ሙላት ዕለት ዕለት በጥልቀት ትለማመዳለህና እግዚአብሔርን አመስግን፡፡
መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን ኢየሱስን የላከልን እግዚአብሔርን ታይ ዘንድ ዓይኖችህን ያብራ፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ሙላት ሊሰጠን ሁሉን ነገር የፈፀመልን መሆኑን ማየት ይሁንልን፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ይህ የአራት ቀናት ዕቅድ ጳውሎስ ወደ ቆላስይስ ሰዎች የፃፈውን ደብዳቤ ይዳስሳል፤ ይኸውም ዓለማትን የፈጠረውና የሰውን ልጅ የታደገው ከሁሉ በላይና ለሁሉ የሚበቃው ኢየሱስ መሆኑን በማስታወስ የሀሰት ትምህርቶችን በመሞገት ነው፡፡ ጳወሎስ ጨምሮም ስለ ቤተሰብ ግንኙነት፣ ፀሎት፣ ቅዱስ አኗኗር እና በፍቅር መታሰር ምን እንደሆነ ተግባራዊ ጥበብን ይሰጣል፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Spoken Gospel ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ http://www.spokengospel.com/