የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ቆላስይስ ሰዎችናሙና

ወደ ቆላስይስ ሰዎች

ቀን {{ቀን}} ከ4

ሐዋርያው ጳውሎስ የቆላስይስ ሰዎች ህያዋን መሆናቸው በክርስቶስ መሆኑን ነግሯቸዋል፡፡ እነርሱ በእግዚአብሔር ሀይል የተሞሉናከሀይላትና ሊቆጣጠራቸውም ከነበረው ምኞት ነፃ የወጡት ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ነፃነት ማህበራዊ ህይወታቸውን፣ የጋብቻ ህይወታቸውን እንዲሁም ተቋማዊ ሁኔታዎቻቸውን አልቀየረውም፡፡ እኚህ አማኞች ያገቡ ናቸው፤ ልጆችም አሏቸው፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ባሪያዎችና የባሪያ አለቆችም ናቸው፡፡ ነገር ግን ጳውሎስ እኚህን መሰል የቤተሰብ ግንኙነት በሚኖሩበት የሮማውያን ግዛት የኢየሱስን ሀይል ለማሳየት ዕድሎች መሆናቸውን ይነግራቸዋል፡፡

ሚስቶች በኢየሱስ በኩል ያገኙትን ነፃነታቸውን አብሯቸው ያለውን ባል ለመተው፣ ለመግፋት ወይም በእርሱ ላይ ለማመፅ መጠቀሚያ ማድረግ የለባቸውም ይልቅ ለባሎቻቸው ታማኞች መሆን አለባቸው፡፡ ባሎችም የስጋ ፍላጎታቸውን ለማርካት ብቻ ሲሉ ነፃነታቸውን መጠቀም የለባቸውም ነገር ግን ሚስቶቻቸውን መውደድና የሚስቶቻቸው ፍላጎት ከእነርሱ ይልቅ ትልቅ መሆኑን መቁጠር ያስፈልጋል፡፡ ልጆች በኢየሱስ ያገኙትን ነፃነት ለወላጆቻቸው ላለመታዘዝ እንደምክንያት መጠቀም የለባቸውም፤ ይልቅ በፍጥነት መታዘዝ ይገባቸዋል፡፡ ወላጆች የሰማዩን አባታቸውን አርዓያነት በመያዝ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ልጆቻቸውን ማበረታታት አለባቸው፡፡ በኢየሱስ ምክንያት ነፃነታቸውን የሚፈልጉ ባሪያዎች ለጌቶቻቸው መታዘዝ ያለባቸው እነርሱን ለማስደሰት ብለው ሳይሆን የመንግሥቱ ወራሾች የሚያደርገውን እግዚአብሔርን ለማስደሰት ነው፡፡ እግዚአብሔር ለባርያም ሆነ ለጌታ በፍፁም አድልዖ አያሳይም፡፡ ስለዚህ የባሪያዎች ጌቶችም ልክ እነርሱ እንደቀጠሯቸው ባሪያዎች ሁሉ እነርሱም ጌታ እንዳላቸው ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ በባሪያዎቻቸው ላይ የበላይ አይደሉም፤ የቀጠሯቸውንም በእኩልነትና በፍትህ መያዝ ካልቻሉ በእነርሱም ላይ ይፈረድባቸዋል፡፡

ጳውሎስ የቆላስይስ ሰዎች ቤቶች የወንጌል ማሳያ ይሆን ዘንድ ይፈልጋል፡፡ ጳውሎስ ግን እንደ ኢየሱስ በትዳር፣ በልጅነትና ሌሎችን በማገልገል መኖር አስቸጋሪ እንደሚሆን ያውቃል፡፡ ጸሎትና ምስጋናንም ይጠይቃል፡፡ እኚህ ጳውሎስ በእስር ሳለ የተማራቸው ናቸው፤ እናም አሁንም ግን ራሱ ልብ ሊላቸው ይገባል፡፡ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ለመፅናት ሁሉም ፀሎት ይፈልጋሉ፡፡ እንዲሁም እግዚአብሔር በቤተሰቦቻቸውና በቤታቸው በኩል ዓለምን ነፃ ለማውጣት ሊገልጥ ስላለው የኢየሱስ ሀይልና ችሎታ ሁሉም የግድ ተስፈኞችና አመስጋኞች መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

በህይወታችን ያሉ ጉልህ የምንላቸው ግንኙነቶቻችን የኢየሱስን ፍቅርና ሀይል ለዓለም ለማንፀባረቅ ታላቅ ዕድሎችን ያቀርቡልናል፡፡ ልክ ሚስቶችመስዋዕት ለሚሆኑላቸው ባሎቻቸው ታማኝነታቸውን ሲገልፁ በአንድነት የቤተክርስቲያን እንዲሁም በገዛ ፈቃዱ የሞተውን የኢየሱስ ፍቅር ህያው ማሳያዎች ይሆናሉ፡፡ ልጆችም ለወላጆቻቸው ሲታዘዙ ኢየሱስ ለአባቱ የታዘዘውን መታዘዝ ያንፀባርቃሉ፡፡ ወላጆች ደግሞ ልጆቻቸውን በትዕግስት ሲያስተምሩ ለማይታዘዘው ዓለም ያለውን የእግዚአብሔርን ትዕግስት ያሳያሉ፡፡ ሌሎችን የሚያገለግሉ ሰዎች እኛን የሚያድነንን የኢየሱስን መሥዋዕታዊ አገልግሎት ያካትታሉ፡፡ እንዲሁም እግዚአብሔርንየሚፈሩ ጌቶች ደግሞ እግዚአብሔር ፍትሕን ለማድረግ ሥልጣኑን የሚጠቀምበትን መንገድ ያንጸባርቃሉ፡፡ የኢየሱስን የምሥራች በግልፅ ለማሳየት ጋብቻ፣ ልጅነት፣ የልጅ አስተዳደግና ሥራ (በከፊል) ይኖራሉ፡፡

ነገር ግን እኚህ ግንኙነቶች የኢየሱስን ሀይልና ፍቅር መግለጫ ብቻም አይደሉም፤ የምንሳተፍባቸው ጭምር ናቸው እንጂ፡፡ ከእኛ ጋር ግንኙነት ያላቸውን እንደምንወዳቸው እኛም የእግዚአብሔርን ፍቅር እንሰጣለን፤ እንቀበላለን፡፡ ጋብቻ፣ ቤተሰብና የስራ ስፍራዎች ከኢየሱስ ጋር ፊት-ለፊት የምንገናኝበት ቅዱስ ቦታዎች ናቸው፡፡ በተለያየ ጊዜያት መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስን እንደ ባል፣ እንደ ልጅ፣ እንደ አባት፣ እንደ ወንድም፣ እንደ ባሪያ እንዲሁም እንደ ጌታ ይገልፀዋል፡፡ ኢየሱስ ራሱን እንደ እናት ሁሉ ይገልፃል፤ ልክ እናት ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ እንደምትጠብቅ ዓይነት፡፡ ጋብቻ፣ ቤተሰቦችና የስራ ቦታዎች ከምናገኛቸው ወሳኝ የእግዚአብሔር ፍቅር መግለጫዎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡መስዋዕት ስናደርግ፣ ስንወድ፣ ስናገለግል፣ ስንታዘዝና ከእኛ ጋር ጓደኞች ለሆኑ ታማኝ ስንሆን እነዚህን ነገሮች ለኢየሱስ እያደረግን ነው፡፡ ሌሎች ደግሞ ለእኛ ይህንኑ ሲያደርጉልን በኢየሱስ ተወደን ነው፡፡

በሌላ ቦታ ጳውሎስ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የሆኑ ህዝቦች የክርስቶስ አካል መሆናቸውን ይገልፃል፡፡ እናም ኢየሱስ እስኪመለስ ድረስ፣ ተመልካቿ ዓለም ለእነርሱ የተሠዋውን የኢየሱስን ሥጋ ሊያዩ የሚችሉበትና የሚለማመዱበት መንገድ ባሎች፣ ሚስቶች፣ ወላጆች፣ ልጆችና ሠራተኞች እርስ በርስ ሲዋደዱና ሲከባበሩ በማየት ነው፡፡

መንፈስ ቅዱስ ነፃነትና ህይወት የሰጠንን እግዚአብሔር ታይ ዘንድ ዓይኖችህን ያበራ ዘንድ እፀልይልሃለሁ፡፡ የእኛን ወሳኝ ግንኙነቶች ፍቅሩንና ሀይሉን ለዓለም ለመግለጥ መጠቀም የሚፈልግ ኢየሱስ መሆኑን ማየት ይሁንልህ፡፡

ቀን 2ቀን 4

ስለዚህ እቅድ

ወደ ቆላስይስ ሰዎች

ይህ የአራት ቀናት ዕቅድ ጳውሎስ ወደ ቆላስይስ ሰዎች የፃፈውን ደብዳቤ ይዳስሳል፤ ይኸውም ዓለማትን የፈጠረውና የሰውን ልጅ የታደገው ከሁሉ በላይና ለሁሉ የሚበቃው ኢየሱስ መሆኑን በማስታወስ የሀሰት ትምህርቶችን በመሞገት ነው፡፡ ጳወሎስ ጨምሮም ስለ ቤተሰብ ግንኙነት፣ ፀሎት፣ ቅዱስ አኗኗር እና በፍቅር መታሰር ምን እንደሆነ ተግባራዊ ጥበብን ይሰጣል፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Spoken Gospel ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ http://www.spokengospel.com/

ተዛማጅ እቅዶች