ወደ ቆላስይስ ሰዎችናሙና
ሐዋርያው ጳውሎስ ደብዳቤውን የሚደመድመው ቀደም ብሎ ያነሳቸውን ሶስት ወሳኝ ነጥቦች ላይ ትኩረት በማድረግ ለቆላሲይስ ሰዎች ሌሎች የግል መልዕክቶችንም በማከል ነው፡፡
ትንሽ ቀደም ባሉት ቁጥሮች ጳውሎስ ባሪያዎች ልክ ኢየሱስን እንደሚያገለግሉ ደስ እያላቸው በፈቃዳቸው ያገለግሉ ዘንድ ነግሯቸዋል፡፡ ለጌቶችም እነርሱ ራሳቸው ጌታ ለሆነው ለእግዚአብሔር ባሪያዎች መሆናቸውን ያሳስባቸዋል፡፡ ስለዚህ ጳውሎስ ቲኪቆስ የሚባለውን አብሮ ሰራተኛ እና አናሲሞስ የተባለውን ያመለጠ ባሪያ ያስተዋውቃቸዋል፡፡ የቆላስይስ ቤተክርስቲያን የሚሰባሰቡት የነበረው በአናሲሞስ ጌታ ቤት የነበረ ስለነበር አናሲሞስ እንደኮበለለ ሁሉም ያውቁ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ጳውሎስ አናሲሞስ ራሱ በገዛ ፈቃዱ እንደ ባሪያ እንኳን ልመለስ ቢል ቤተክርስቲያን ግን ዳግም እንደ ወንድም እንድትቀበለው ይነግራቸዋል፡፡ በዚህ መግቢያ ላይ ጳውሎስ የቆላስይስ ቤተክርስትያን ባይተገበር ዋጋ የሚያስከፍልን ውድ የሆነ በግንኙነት ውስጥ ያለን የቤተሰብ ፍቅርን እንድትለማመድ ዘርግቷል፡፡
ቀደም ብሎ ጳውሎስ እግዚአብሔርን ለማስደሰት የአይሁድም ሆነ የአህዛብ መንገድ የሚባል ነገር እንደሌለ ለማስረገጥ ረጅም ርቀት ሄዷል፡፡ ሁሉም ሰዎች በእግዚአብሔር ፍጥረትነት አንድ የሆኑ እንዲሁም ሁሉም ሰዎች በኢየሱስ ብቻ የዳኑ ናቸው፡፡ ስለዚህ ጳውሎስ አብረውት የሚሰሩትን ሦስት የአይሁዳውያንን እንዲሁም ሦስት የግሪካውያን ስም በመጥቀስ ሰላምታቸውን ያሰፍራል፡፡ የእነዚህ የ6ቱ ሰዎች ስም ለቆላሲይስ ሰዎች የሚያሳስባቸው እነርሱ ሰዎችን ሁሉ በድነት አንድ ለማድረግ የኢየሱስ ዕቅድ አካል መሆናቸውን ነው፡፡
ጳውሎስ በደብዳቤው ሁሉ የቆላስይስ ሰዎች በኢየሱስ ትምህቶች ማደግ እንደሚገባቸው ትኩረት ይሰጣል፡፡ የኢየሱስን መልዕክቶች በጥልቀት በማጥናት የቆላሲይስ ሰዎች የእግዚአብሔርን ሙላት እንደሚለማመዱና የኢየሱስን ህይወት እንደሚያንፀባርቁ ጳውሎስ ያውቃል፡፡ ስለዚህ ጳውሎስ የቆላሲይስ ቤተክርስቲያንን የመሰረተውን ኤጳፍራን ያነሳል፡፡ ኤጳፍራ ጳውሎስን በእስር ሳለ ለማበርታት እንዲሁም ስለተከላት ቤተክርስቲያን ምክር ለመጠየቅ ተጉዟል፡፡ በዚያ ወቅት ጳውሎስ ኤጳፍራ ለቆላሲይስ ሰዎች ጥልቅ ፍቅር እንደነበረውና ለኢየሱስ ባለቸው መሰጠት ወደ ብስለት ይመጡ ዘንድ ከልቡ ሲፀልይላቸው ተመልክቷል፡፡ እንደ ሐዋርያነቱ ጳውሎስ ይህንን ሸክም ተካፍሎታል፡፡ ኤጳፍራ ወደ ብስለት ስለመምጣት ያቀረበውን ጸሎት የቆላስይስ ሰዎች እንዲሁም ክርስቲያኖች ወደ ኢየሱስ እውነትና ሕይወት ጠለቅ ብለው እንዲሄዱ የሚያስፈልጓቸውን ውጤታማ መንገዶች በመጥቀስ የጻፈውን መልዕክት ይደመድማል፡፡
የበሰለ የኢየሱስ ተከታይ በኢየሱስ ብቻ መዳኑን የሚቀበል እንዲሁም የሚገባው እንደሆነ እንኳን እያወቀ በመስዋዕትነት ይወዳል፡፡ እነዚህ ለመኖር ከባድ የህይወት ትምህርቶች ናቸው ነገር ግን የቆላስይስ ሰዎች መጽሐፍ የሚቋጨው በተስፋ ማለትም ተስፋው እንደ ኢየሱስ ተከታይ ማደግ እንደሚቻል በማሳየት ነው፡፡
ጳውሎስ ከጻፋቸው የግል መልዕክቶቹ ሁሉ አስቀድሞ እግዚአብሔርን ለመምሰል ወደ ብስለት ለመምጣት ተስፋ ማድረግ እንችላለን፡፡ የእግዚአብሔር ሃይል ሙላት በውስጣችን ይኖራል፡፡ አሮጌው፣ ሙቱና ሃጥያተኛው ማንነታችን በመስቀል ላይ ተጠርቋል፡፡ እኛ ሁላችን ስላለፉት በደሎቻችን ይቅርታን አግኝተናል፡፡ በሃጥያት ምክንያት የመጣብን ሃፍረት ተሸንፏል ምክንያቱም በኢየሱስ በኩል ውርደቶቻችን የትንሳዔ መገለጫ ይሆናሉ፡፡
በኢየሱስ ቀን በቀን እንዲሁም ደረጃ በደረጃ ወደ ኢየሱስ መልክ እያደጋችሁ ነው፡፡ በየጊዜው ኢየሱስ ለአንተ ስላደረገው ነገር ባሰብክ ቁጥር ወደ ብስለት እየመጣህ መሆንህን እርግጠኛ ሁን፡፡ አሁን ላይ የሆነ ጊዜ ላይ የነበርከውን ዓይነት ሰው አይደለህም፡፡ ምንም የተለወጠ ነገር ያለ እስከማይመስልህ እንዲሁም የዛሬ ሦስት ዓመት በፊት እንደነበርከው ዓይነት ሰው ስሜት ቢሰማህ ያ እውነት አይደለም፡፡ በኢየሱስ ላይ ዓይኖችህን ማድረግህን በቀጠልክ ቁጥር እርሱ ወደ ብስለት ሊያደርስህ ቃል ገብቷል፡፡
የሚለውጠንን እግዚአብሔርን ታዩ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ዓይናችሁን እንዲያበራላችሁ እጸልያለሁ፡፡ እንዲሁም ኢየሱስ የእርሱን መልክ በመምሰል እንድታድጉ፣ ሁልጊዜም ያደረገላቸሁን የምታስቡ ያድርጋችሁ፡፡
ስለዚህ እቅድ
ይህ የአራት ቀናት ዕቅድ ጳውሎስ ወደ ቆላስይስ ሰዎች የፃፈውን ደብዳቤ ይዳስሳል፤ ይኸውም ዓለማትን የፈጠረውና የሰውን ልጅ የታደገው ከሁሉ በላይና ለሁሉ የሚበቃው ኢየሱስ መሆኑን በማስታወስ የሀሰት ትምህርቶችን በመሞገት ነው፡፡ ጳወሎስ ጨምሮም ስለ ቤተሰብ ግንኙነት፣ ፀሎት፣ ቅዱስ አኗኗር እና በፍቅር መታሰር ምን እንደሆነ ተግባራዊ ጥበብን ይሰጣል፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Spoken Gospel ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ http://www.spokengospel.com/