1
የዮሐንስ ወንጌል 6:35
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፤ በእኔ የሚያምንም ለዘለዓለም አይጠማም።
موازنہ
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 6:35
2
የዮሐንስ ወንጌል 6:63
ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ግን አንዳች አይጠቅምም፤ ይህም እኔ የምነግራችሁ ቃል መንፈስ ነው፤ ሕይወትም ነው።
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 6:63
3
የዮሐንስ ወንጌል 6:27
የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘለዓለም ሕይወት ለሚኖር መብል ሥሩ እንጂ ለሚጠፋው መብል አይደለም፤ ይህን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 6:27
4
የዮሐንስ ወንጌል 6:40
የአባቴ ፈቃዱ ይህ ነው፤ ወልድን አይቶ የሚያምንበት ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኝ ነው፤ እኔም በመጨረሻዪቱ ቀን አስነሣዋለሁ።”
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 6:40
5
የዮሐንስ ወንጌል 6:29
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው ታምኑ ዘንድ ነው፤” አላቸው።
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 6:29
6
የዮሐንስ ወንጌል 6:37
አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ ወደ እኔ የሚመጣውንም ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም።
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 6:37
7
የዮሐንስ ወንጌል 6:68
ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ እንዲህ አለው፥ “አቤቱ፥ የዘለዓለም የሕይወት ቃል እያለህ ወደ ማን እንሄዳለን?
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 6:68
8
የዮሐንስ ወንጌል 6:51
“ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ከዚህ እንጀራ የሚበላ ለዘለዓለም ይኖራል፤ ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው ይህ እንጀራ ሥጋዬ ነው።”
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 6:51
9
የዮሐንስ ወንጌል 6:44
የላከኝ አብ ካልሳበው በቀር ወደ እኔ መምጣትን የሚችል የለም፤ እኔም በመጨረሻዪቱ ቀን አስነሣዋለሁ።
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 6:44
10
የዮሐንስ ወንጌል 6:33
የእግዚአብሔር እንጀራ ከሰማይ የሚወርድ፤ ለዓለምም ሕይወትን የሚሰጥ ነውና።”
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 6:33
11
የዮሐንስ ወንጌል 6:48
የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ።
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 6:48
12
የዮሐንስ ወንጌል 6:11-12
ጌታችን ኢየሱስም ያን እንጀራ ይዞ አመሰገነ፤ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ደቀ መዛሙርቱም ለተቀመጡት ሰዎች ሰጡአቸው፤ ከዓሣውም እንዲሁ የፈለጉትን ያህል ሰጡአቸው። ከጠገቡም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን፥ “ከቍርስራሹ ምንም የሚወድቅ እንዳይኖር የተረፈውን ቍርስራሽ አንሡ፤” አላቸው።
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 6:11-12
13
የዮሐንስ ወንጌል 6:19-20
ሃያ አምስት ወይም ሠላሳ ምዕራፍ ያህል ከሄዱ በኋላ ጌታችን ኢየሱስን በባሕር ላይ ሲሄድ አዩት፤ ወደ ታንኳዉ በቀረበ ጊዜም ፈሩ። እርሱም፥ “እኔ ነኝ፤ አትፍሩ” አላቸው።
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 6:19-20
صفحہ اول
بائبل
مطالعاتی منصوبہ
Videos