1
ትንቢተ ሕዝቅኤል 34:16
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
የጠፋውንም እፈልጋለሁ፤ የባዘነውንም እመልሳለሁ፤ የተሰበረውንም እጠግናለሁ፤ የደከመውንም አጸናለሁ፤ የወፈረውንና የበረታውንም እጠብቃለሁ፤ በፍርድም እጠብቃቸዋለሁ።”
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ሕዝቅኤል 34:12
በደመናና በጭጋግ ቀን እረኛ ከበጎቹ መካከል የተለየውን እንደሚፈልግ፥ እንደዚሁ በጎችን እፈልጋለሁ፤ በደመናና በጭጋግ ቀን ከተበተኑባቸው ሀገሮች ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ።
3
ትንቢተ ሕዝቅኤል 34:11
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ራሴ በጎችን እሻለሁ፤ እጐበኛቸዋለሁም።
4
ትንቢተ ሕዝቅኤል 34:15
እኔ ራሴ በጎችን አሰማራለሁ፤ አስመስጋቸውማለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
5
ትንቢተ ሕዝቅኤል 34:31
እናንተም በጎች፥ የማሰማሪያዬ በጎች፥ ሰዎች ናችሁ፤ እኔም አምላካችሁ ነኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”
6
ትንቢተ ሕዝቅኤል 34:2
“የሰው ልጅ ሆይ! ትንቢት ተናገር፤ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፤ እረኞችንም እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ራሳቸውን ለሚያሰማሩ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው! እረኞች ራሳቸውን ያሰማራሉን? እረኞች በጎችን ያሰማሩ ዘንድ አይገባቸውምን?
Home
Bible
Plans
Videos