ኦሪት ዘፍጥረት 8:1-22

ኦሪት ዘፍጥረት 8:1-22 አማ54

እግዚአብሔርም ኖኅን፤ በመርከብም ከእርሱ ጋር የነበረውን አራዋቱን ሁሉ፤ እንስሳውንም ሁሉ አሰበ። እግዚአብሔርም በምድር ላይ ነፉስን አሳለፈ፤ ውኂውም ጎደለ የቀላዪም ምንጮች የሰማይም መስኮቶች ተደፈኑ፤ ዝናብም ከሰማይ ተከለከለ ውኂውም ከምድር ላይ እያደር እያደር ቀለለ፤ ከመቶ አምሳ ቀንም በኋላ ውኂው ጎደለ። መርከቢቱም በስባተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሰባተኛው ቀን በአራራት ተራሮች፤ ላይ ተቀመጠች። ውኂውም እስከ አሥረኛው ወር ድረስ ይጎድል ነበረ፤ በአሥረኛው ወር ድረስ ይጎድል ነበር በአሥረኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የተራሮች ራሶች ተገለጡ። ከአርባ ቀንም በኋላ ኖኅ የሠራውን የመርከቢቱን መስኮት ከፈተ፤ ቁራንም ሰደደው እርሱም ወጣ፤ ውኂው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ ወዲያና ወዲህ ይበር ነበር። ርግብንም ውኃው ከምድር ፊት ቀልሎ እንደ ሆነ እንድታይ ከእርሱ ዘንድ ሰደዳት። ነገር ግን ርግብ እግርዋን የምታሳርፍበት ስፍራ አለገኘችም፤ ወደ እርሱም ወደ መርከብ ተመለሰች ውኃ በምድር ላይ ሁሉ ስለ ነበረ እጁን ዘረጋና ተቀበላት ወደ እርሱም ወደ መርከብ ውስጥ አገባት። ከዚያም በኋላ ደግሞ እስከ ስባት ቀን ቆየ ርግንም እንደ ገና ከመርከብ ሰደደ። ርግብም በማታ ጊዜ ወደ እርሱ ተመለሰች በአፍዋም እነሆ የለመለመ የወይራ ቅጠል ይዛ ነበር። ኖኅም ከምድር ላይ ውኃ እንደ ቀለለ አወቀ። ደግሞ እስከ ሰባት ቀም ቆየ ርግብንም ሰደዳት ዳግመኛም ወደ እርሱ አልስተመለሰችም። በኖኅ ዕድሜ በስድስት መቶ አንድ ዓመት በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ውኃው ክዳን አነሣ፥ እነሆም ውኃው ከምድር ፊት እንደ ደረቀ አየ። በሁለተኛውም ወር ከወሩም በሀያ ሰባተኛውም ወር ቀን ምድር ደረቀች። እግዚአብሔርም ለኖኅ እንዲህ ብሎ ነገረው፥ አንተ ሚስትህንና ልጆችህን የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ከመርከብ ውጣ። ከአንተ ጋር ያሉትን አራዊት ሁሉ ሥጋ ያላቸውን ሁሉ፥ ወፎችንና እንስሶችን ሁሉ፥ ከአንተ ጋር አውጣቸው በምድር ላይ ይብዙ። ኖኅም ልጆቹንና ሚስቱን የልጆቹንም ሚስቶች ይዞ ወጣ። አራዊት ሁሉ፥ ተቀሳቃሾች ሁሉ፥ ወፎችም ሁሉ በምድር ላይ የሚርመሰምስው ሁሉ በየዘመዳቸው ከመርከብ ወጡ። ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያውን ሠራ፥ ከንጽሕም እንስሳ ሁሉ ከንጹሐን ወፎችን ሁሉ ወሰደ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀርበ። እግዚአብሔርም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፥ ምድርን ዳግመኛ ስለ ስው አልረግምም፥ የሰው ልብ አሳብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፉ ነውና ደግሞም ከዚህ ቀድሞ እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉት እንደ ገና አልመታም። በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም።