መጽሐፍ ቅዱስ ህያው ነውናሙና
መጽሐፍ ቅዱስ ህያው ነው መጽ
ሐፍ ቅዱስ ለእኛ የእግዚአብሔር ቃል ነው። እግዚአብሔር የሰውን ዘር ለማዳን እና ለመመለስ ስለ ራሱ ባህሪይ፣ እና እቅዶች በሰዎች በኩል የተናገረው ንግግር ነው። በእግዚአብሔር የተሰጠ ስለሆነ፣ እያንዳንዱ ክፈል እኛን ለመምከር፣ ለመገሰጽ እና ለመለወጥ ሀይል አለው። ህይወትዎ እየታደሰ የነበረበትን ወቅት ወይም የተወሰነ የህይወትዎ ክፍል እየ
B6ታደሰ የነበረበትን ጊዜ አስቡ። መጽሐፍ ቅዱስን በየጊዜው የሚያነቡ ወይም የሚያዳምጡ ከሆነ፣ ለማስተማር፣ ለማበረታታት እና ለመገሰጽ ያለውን ሃይል ተለማምደዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ከታሪክ ትምህርት ያለፈ ነው። ምንም እግዚአብሔር ያደረገውን ቢናገርም፣ እግዚአብሔር ወደፊት የሚያደርገውንም ያሳየናል። እግዚአብሔር በታሪክ ውስጥ የገለጠውን ትርክ
ት ይገልጣል፤ በእኛ ውስጥም ይህን ታሪክ መናገር ይፈለጋል። የእግዚአብሔር ቃል ከጊዜ መጀመሪያ ጀምሮ በሰዎች ልብ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ከተማዎችን፣ ህዝቦችን እና አህጉራትን ለውጧል። ስለዚህ በዚህ ሳምንት፣ መጽሐፍ ቅዱስ በአለማችን ላይ እንዴት ህያው እና እየሰራ እንደሆነ በታሪክ ውስጥ እግዚአብሔር ለክርስሪያኖች
የተናገረውን በማየት እናከብራለን—ይህም ትርክት መጽሐፍ ቅዱስ ጨለማን እንዴት እንደሚገፍ፣ ተስፋን እንደሚሰጥ፣ ህይወቶችን እንደሚያድስ እና አለምን እንደሚቀይር የሚናገር ነው።
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ከጊዜ መጀመሪያ ጀምሮ፣ የእግዚአብሔር ቃል በትጋት ልቦችን እና አእምሮዎቸን አድሷል—እና እግዚአብሔር አሁንም አልጨረሰም። በዚህ የ 7 ቀን እቅድ፣ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስን በመጠቀም ታሪክ እየሰራ እና በአለም ዙሪያ ህይወቶችን እንዴት እየቀየረ እንዳለ በቅርበት በመመልከት የመጽሐፍ ቅዱስን ህይወት ቀያሪነት እናከብራለን።
More
ይህ ዋናው የመጽሐፍ ቅዱስ እቅድ የተሰራው እና የቀረበው በ YouVersion ነው።