መጽሐፍ ቅዱስ ህያው ነውናሙና

መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉንም እየቀየረ ነው እግዚአብሔር "
ብርሃን ይሁን" የሚለውን ቃል እስከሚናገር ድረስ ሁሉም ነገር ጨልሞ እን ቅርጽ አጥቶ አስቡት እስቲ። በመቅጽበት፣ ሁሉም ነገር ተቀየረ። ብርሃኑ ጨለማውን ገፈ
ፈው፣ በፊት የማይታይ የነበረ አሁን በግልጽ ይታያል። ከእግዚአብሔር የወጣ አንድ ቃል ሁሉንም ቀየረው … ነገር ግን እዚያ ላይ አላቆመም። አለምን ሁሉ በአንድ እስትንፋስ የቀየረ እግዚአብሔር በቃሉ ሃይል አለም ላይ አዲስ ህይወትን አሁንም እየተነፈሰ ነው። የእግዚአብሔር ቃል ጨለማውን መግፈፍ አሁንም ቀጥሏል። የእግዚአብሔር ቃል ህይወቶችን ይቀይራል እና የተጎዱ ልቦችን ያድሳል። የእግዚአብሔር ቃል
ህያው እና የሚሰራ የሆነው እርሱ ህያው እና የሚሰራ ስለሆነ ነው። እና ቃሉን ሁልጊዜ ማግኘት እንችላለን። መጽሐፍ ቅዱስን ባጠናን ቁጥር፣ እግዚአብሔር በአለም ያሉትን ሁሉ ከእርሱ ጋር የግል፣ የሚሰራ እና የሚያድስ ግንኙነት አንዲኖራቸው እንደሚፈልግ እንረዳለን። ምንም አይነት ችግር እና ፈተና ቢገጥመን፣ የእግዚአብሔር ቃል ጨለማውን መግፈፉን ይቀጥላል።
የእርሱ ቃል እንደ ጋና፣ ሱሙ፣ የፖፖሉካ ሰዎችን፣ ሳሙኤል አጃዪ ክራውተር፣ እና ዊሊያም ቲንዴል ያሉ ሰዎችን መለወጡን ይቀጥላል። የእርሱ ቃል አንተን የመቀየር ሃይል አለው። ስለዚህ ቆም ብለህ ስለራስህታሪከ አስብ። የእግዚአብሔር ቃ
ል ለውጦሃል? እና በምን መንገዶች እግዚአብሔር በህይወትህ ውስጥ ቃሉን ህያው ያድርገው? እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር በህይወትህ የሰራውንአመስግን፣ እና በአንተ አካባቢ ባለው ላይ ምን እያደረገ እንደሆነ አስተውል። ከዚህ በኋላም እግዚአብሔር እየተናገረ
ባለው ታሪክ ላይ ተሳታፊ ሁን። አለምን ካለመኖር ወደመኖር ሲያመጣ ጀምሮ የጀመረ ታሪክ ነው፣ እና ኢየሱስ እስከሚመጣ ቀን ድረስ ይቀጥላል—የኋላ ታሪክን ያለፈ እና አለምን እየቀየረ ያለ ታሪክ።ስለዚህ እቅድ

ከጊዜ መጀመሪያ ጀምሮ፣ የእግዚአብሔር ቃል በትጋት ልቦችን እና አእምሮዎቸን አድሷል—እና እግዚአብሔር አሁንም አልጨረሰም። በዚህ የ 7 ቀን እቅድ፣ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስን በመጠቀም ታሪክ እየሰራ እና በአለም ዙሪያ ህይወቶችን እንዴት እየቀየረ እንዳለ በቅርበት በመመልከት የመጽሐፍ ቅዱስን ህይወት ቀያሪነት እናከብራለን።
More
ይህ ዋናው የመጽሐፍ ቅዱስ እቅድ የተሰራው እና የቀረበው በ YouVersion ነው።