መጽሐፍ ቅዱስ ህያው ነውናሙና
መጽሐፍ ቅዱስ ጨለማን ይውጣል ሱሙ ከክርስ
ትና ጋር በተያያዘ ምንም ነገር ማድረግ አትፈልግም ነበር። ነገር ግን በ 2017፣ የሱሙ ጓደኛ ምስክርነቷን በኒውዚላንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሰጠች። ሱሙ አብራተ ልትቆም መጣች …እና መላልሳ መምጣት ጀመረች። ወደ ህንድ ከመሄዷ በፊት.
በዚያን አመት ህይወቷን ለኢየሱስ ሰጠች። አዲስ. እምነትን በአዲስ ሀገር ውስጥ ያለ ክርስቲያኖች ህብረት መግፋት በጣም ከባድ ነው፣ እና ሱሙ በጣም ከባድ ድብርት ውስጥ ገብታ በየቀኑ ከአልጋ መውጣት ከበዳት። "በጣም ብቸኛ ሆኜ ከሰዎች ጋር መግባባት በጣም ከበደኝ። ወደ ህንድ ስመጣ ራሴን መቻል በጣም ከብዶኝ ብዙ መ
ጥፎ ሃሳቦች ወደ አእምሮዬ ገቡ። ነገር ግን በ YouVersion ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ስገናኝ ነበር አስተሳሰቤን መቀየር የቻልኩት።" YouVersion ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር መገናኛ መንገድ በመክፈት በመጽሐፍ ቅዱስ እቅዶች ከእነርሱ መማር ቻለች። እና ከ 2018 ጀምሮ ከ 428 በላይ የሆኑትን ጨርሳለች። በየትኛውም ጊዜ ሱሙ ጥያቄ ሲኖራት፣ YouVersion መተግበሪያዋን ከፍታ በዚያ ርእስ ላይ እቅዶችን ትፈለጋለች። ብዙ እቅዶችን ባነበበች ቁጥር፣ እምነቷ በብዙ ይጨምራል። "አንዳንድ ቀናት 11 እቅዶችን በመጀመር በእውነት ውስጥ ራሴን ለመክተት እሞክራለሁ። አንተ ባለፍክበት መንገድ ከተጓዙ ሰዎች መማር እና ማበረታቻ ማግኘት እድል ነው። በትግሎቼ ውስጥ ብቻዬን እንዳልሆንኩኝ ተምሬያለሁ። ድብርት ውስጥ የነበሩ እና ከዚያ ከወጡ ሰዎችን በመስማት የኢየሱስ ተከታዮችም የአእምሮ ጤና ችግር ውስጥ እንደሚያልፉ መገንዘብ ችያለሁ።" አሁን ሱሙ ብቸኝነት ሲሰማት፣ ሲደብራት ወይም ከሰው ስትለይ የእግዚአብሔርን ተስፋ ቃሎች በመያዝ ሃሳቦቿን በሙሉ ኢየሱስ ስለ እርሷ በሚለው ትሞላዋለች። "አንዳንድ ጊዜ፣ ሲደብርህ፣ የሚያስፈልግህ ቃል ነው። መተግበሪያው መጽሐፍ ቅዱስን እና እምነቴን እንዳውቅ የረዳኝ "አቋራጭ መንገድ" ነው። ቴክኖሎጂ ከእምነታችና ጋር እንድንገናኝ የሚያደርገን ምርጥ መሳሪያ ነው። ከክርስቶስ ጋር የምገናኝበት መንገድ ባይኖረኝ እስከአሁን እቆያለሁ ብዬ አላስብም፣ ምክንያቱም እነዚያ ቀናት በጣም ጨለማ ነበሩ እና የነበረኝ ብቸኛ የብርሃን ምንጭ እርሱ ነበር—አሁንም እርሱ ነው። በእግዚአብሔር ቃል ሃይል አማካኝነት፣ ከሰው መገለል ወደ መቀራረብ ይቀየራል፣ በመከራ ውስጥ ተስፋን ማግኘት ይቻላል። የሱሙን ህይወት አንድ ጊዜ አስቡት፣ እና አሁን ስላላችሁበት የህይወት መንገድ እግዚአብሔርን አውሩት። ይህን እያደረጋችሁ፣ ስለሁኔታችሁ እውነታ እግዚአብሔር እንዲገልጥላችሁ ጠይቁት እና ተስፋና ማበረታቻ ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስን አስሱ። የእርሱ መብራት በህይወታችሁ ያለውን ምንም ጨለማ አልፎ እንዲሄድ ፍቀዱ።ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ከጊዜ መጀመሪያ ጀምሮ፣ የእግዚአብሔር ቃል በትጋት ልቦችን እና አእምሮዎቸን አድሷል—እና እግዚአብሔር አሁንም አልጨረሰም። በዚህ የ 7 ቀን እቅድ፣ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስን በመጠቀም ታሪክ እየሰራ እና በአለም ዙሪያ ህይወቶችን እንዴት እየቀየረ እንዳለ በቅርበት በመመልከት የመጽሐፍ ቅዱስን ህይወት ቀያሪነት እናከብራለን።
More
ይህ ዋናው የመጽሐፍ ቅዱስ እቅድ የተሰራው እና የቀረበው በ YouVersion ነው።