መጽሐፍ ቅዱስ ህያው ነውናሙና
መጽሐፍ ቅዱስ ሃገራትን ይለውጣል በ 1800ዎቹ
መጀመሪያ ነበር የ 12 አመት ናይጄሪየዊ ወንድ ልጅ እና ቤተሰቡ ወደ አሜሪካ በፖርቹጋል የባሪያ መርከብ ተወሰዱ። ነገር ግን መርከቡ የአፍሪካ ክልልን ሊለቅ ሲል በጸረ-ባሪያ ተቆጣጣሪዎች ተከቦ ህገወጥ አዘዋዋሪዎቹ በቁ
ጥጥር ስር ውለዋል። ልጁ እና ቤተሰቡ ነጻ ወጥተው ወደ ሴራሊዮን ተላኩ። እዚህ ነበር የመጽሐፍ ቅዱስን ሃይል ያገኘው። ክርስቲያን ከሆነ በኋላ፣ ሳሙኤል አጃዪ ክሮውተር ብዙ ቋንቋዎችን በመማር በሴራሊዮን አካባቢ ወደሚገኙ ሀገሮች በመሄድ የሚሽነሪ ስራዎችን የሰራው። ይህን ሁሉ ጊዜ ግን መጽሐፍ ቅዱስ በናይጄሪያ ቋንቋ—በዮሩባ ስላልነበረ ያጠናው በእንግሊዝኛ ነበር። ይህ ማለት በናይጄሪያ ያሉ እንግሊዝኛ መናገር የማይችሉ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል በራሳቸው ማንበብ አይችሉም ማለት ነው። ስለዚህ አጃዪ በዮሩባ የሰዋሰው ስርአት በመጻፍ እገዛ በማድረግ መጽሐፍ ቅዱስን ወደዚያ ቋንቋ ተርጉሟል። የዮሩባ መጽሐፍ ቅዱስን ከጨረሰ በኋላ፣ ሰዎች እርሱ ያገኘውን ህየወትቀያሪ ተሞክሮ እንዲያገኙ መጽሐፍ ቅዱስን ወደሌሎች የናይጄሪያ ቋንቋዎች መተርጎም ቀጠለ። በኋላ ላይም ክራውተር በአንግሊካል ቤተክርስቲያን "የኒጀር ቢሾፕ" በመሆን የመጀመሪያው አፍሪካዊ የአንግሊካል ቢሾፕ ሆኖ ተ
መረጠ። እና ዛሬ በናይጄሪያ ያለው አንግሊካል ቤተክርስቲያን ከ 18 ሚሊዮን በላይ የተጠመቁ አባላት ያሉት ሁለተኛው ትልቅ አንግሊካን ክልል ነው። በክራውተር የሰራው ራሱ እግዚአብሔር በአንተ ውስጥ በመስራት በቃሉ በኩል አለም ላይ ተጽእኖ ማምጣት ይፈልጋል። አንተ ብቻ ልትደርስባቸው የምትችላቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ሊለወጡ የሚችሉ እየጠበቁ ያሉ ሰዎች አሉ። ስሊዚህ ዛሬ፣ እየተናገረ ባለው ታሪክ ውስጥ መጫወት የምትችለው ሚናንእንዲገልጥልህ እግዚአብሔርን ጠይቅ፣ እና ከጠየከው፣ ካሰብከው ወይም ከገመትከው በላይ በህይወትህ ሲያደርግ ተመልከት።
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ከጊዜ መጀመሪያ ጀምሮ፣ የእግዚአብሔር ቃል በትጋት ልቦችን እና አእምሮዎቸን አድሷል—እና እግዚአብሔር አሁንም አልጨረሰም። በዚህ የ 7 ቀን እቅድ፣ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስን በመጠቀም ታሪክ እየሰራ እና በአለም ዙሪያ ህይወቶችን እንዴት እየቀየረ እንዳለ በቅርበት በመመልከት የመጽሐፍ ቅዱስን ህይወት ቀያሪነት እናከብራለን።
More
ይህ ዋናው የመጽሐፍ ቅዱስ እቅድ የተሰራው እና የቀረበው በ YouVersion ነው።