መጽሐፍ ቅዱስ ህያው ነውናሙና
መጽሐፍ ቅዱስ ተስፋን ያመጣል ጋና
* በ2016 ህይወትን የሚቀይረውን የኢየሱስ ሃይል እስከምታገኝ ድረስ ታታሪ ሙስሊም ነበረች። ነገር ግን ክርስቲያን ከሆነች በኋላ፣ በማህበረሰቧ እና በቤተሰቧ ተጣለች፣ ተተወች፣ እና ተገለለች። የሆነ ወቅት፣ ልጆቿ ከእርሷ ተወስደው ወደሌላ ሃገር ተላኩ። ምንም ጋና ኢየሱስን መካድ እምቢ ብትልም፣ በእምነቷ እንድትበረታ ግን ጠን
ካራ መሰረት አላገኘችም። ብቸኟ ሆና እና ተደብራ ራሷን ማጥፋት አስባ ነበር። ነገር ግን በስልኳ ላይ YouVersion የሚያወርድላት አንድሰው አገኘች። በመጀመሪያ ጋና ፈላጎት አልነበራትም፣ ነ
ገር ግን የእለቱን ጥቅስ በየጠዋቱ በማንበብ ቀኑን እያሰበችው እና ለምሪት እየተጠቀመችው መምጣት ጀመረች። ከጊዜ በኋላ ያልተጠበቀ ነገር ሆነ… "ጥቅሶቹ ህያው ሆነው በእኔ ውስጥ መኖር ጀመሩ። ከሰዎች ጋር ጤናማ በሆነ መንገድእንዴት መኖር እንዳለብኝ አሰተማሩኝ፣ እና ከድብርት እንደወጣ ረዱኝ። ምንም የተገለልኩ ብሆንም፣ በማነብበት ወቅት እረፍት ይሰማኛል። የየቀኑን ጥቅስ ባነበኩ ጊዜ፣ በሆነ መንገድ ከፍ ያደርገኝ እና ተስፋን ይሰጠኛል። እግዚአብሔር በጥቅሶቹ አማካኝነት በቀጥታ የሚናገረኝ ነው የሚመስለው።" ጋና አሁን በሄደችበት ሁሉ የእለቱን ጥቅስ ለሰዎች የምታጋራበትን እድል ትፈለጋለች። ማህበረሰቧን ለማበረታታት ጥቅሶችን በመስመር ላይ ትለጥፋለች፣ እና በስራ ቦታ ለባልደረቦቿ እና ለደንበኞቿ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ታወራለች። የእርሷ ታሪክ በሁላችንም ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል ምን መስራት አንደሚችል አንድ ምሳሌ ነው። ሁኔታዎች ሊቀየሩ ይችላሉ፣ ስሜቶች ሊወጡና ሊወርዱ ይችላሉ፣ ሰዎች ሲያበሳጩን ወይም ሊተዉን ይችላሉ—ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ለዘላለም ይኖራል። እና በዚህ ምክንያት ሁኔታዎቻችንን የሚያልፍ ሰላም እና ተስፋ መለማመድ እንችላለን። ምክንያቱን የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ልባችን እንዲገባ ስንፈቅድ፣ በዚያ ይቆያል። ዛሬ፣ እግዚአብሔር ቃሉን ወደ ህይወታችሁ እንዲያስገባ ይህን ጸሎት ይጸልዩ፡ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ፈጥረኸኛል እና ታውቀኛለህ። ህይወቴን መለወጥ ብቻህን ሃይል ያለህ አንተ ነህ። ዛሬ የምለምንህ ህይወቴን ከቃልህ ጋር አንድ እንድታደርገው ነው። ምንም ነገር ቢገጥመኝ፣ ለቃልህ ታማኝ የምሆንበትን ድፍረት ስጠኝ እና በህይወቴ ላስቀመጥካቸው ሰዎች እውነትህን እና ፍቅርህን እንዳወራ እርዳኝ። ወደ አንተ ስጠጋ የእምነቴ ስር በጥልቀት እንዲሰድ አድርግ። በኢየሱስ ስም፣ አሜን። *የሰውየውን ማንነት ለመጠበቅ ስሙ ተቀይሯል።
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ከጊዜ መጀመሪያ ጀምሮ፣ የእግዚአብሔር ቃል በትጋት ልቦችን እና አእምሮዎቸን አድሷል—እና እግዚአብሔር አሁንም አልጨረሰም። በዚህ የ 7 ቀን እቅድ፣ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስን በመጠቀም ታሪክ እየሰራ እና በአለም ዙሪያ ህይወቶችን እንዴት እየቀየረ እንዳለ በቅርበት በመመልከት የመጽሐፍ ቅዱስን ህይወት ቀያሪነት እናከብራለን።
More