BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎችናሙና
ጳውሎስ በደብዳቤዎቹ ስለእግዚአብሔር ፍቅር ያለውን ምልከታዎች አስቀምጧል። ፍቅሩ ከአይሁድ የሚያልፍና አህዛብንም የሚያካትት እንደሆነና ምንም ነገር የእግዚአብሔርን ህዝብ ከእርሱ ፍቅር ሊለይ እንደማይችል አስተምሯል። ጳውሎስ በአንዱ ደብዳቤው የኢየሱስ ፍቅር እጅግ ታላቅ ከመሆኑ የተነሳ ሰዎች እንዲረዱት እና እንዲደገፉበት መለኮታዊ እገዛ እንደሚያስፈልጋቸው ያስተውላል። ከዚያም ጳውሎስ አንባቢዎቹ በእግዚአብሄር መንፈስ እንዲጠነክሩ ይጸልያል።
ያንብቡ፦
ኤፌሶን 3÷14-21፣ ሮሜ 8÷38-39
ምልከታዎን ያስፍሩ፡
የቀኑን ምንባብ በጥንቃቄ ያንብቡ። ጳውሎስ ለሚጠቀማቸው ቃላትና ዘይቤዎች ትኩረት ይስጡ። ምን ያስተውላሉ?
እርስዎ ራስዎ (ወይም የሚያውቁት ሰው) የእግዚአብሔርን ፍቅር ከመቀበል የሚከለክል መልኩ እጅግ የበዛ ሀጥያት እንደሰሩ አስበው ያውቃሉ? ሀጥያታችን ረዥምና ጥልቅ ሊሆን ይችላል፣ የኢየሱስ ፍቅር ከዚያም ከፍ ያለ ነው። በሌላ አባባል፣ ከምናስበው በላይ ሀጥያት ባለበት፣ የኢየሱስ ፍቅር ከምናስበው በላይ ይቅርታ ያደርጋል። የእግዚአብሔርን ፍቅር በጥረታችን አናገኘውም፣ ፍቅሩን ለመቀበል ማድረግ የምንችለው ራሳችንን በትህትና ዝቅ ማድረግ ነው። ይህን መልካም ዜና ማስታወስ የሚያስፈልገው ሌላ ሰው ማን ነው ብለው ያስባሉ?
ምልከታዎን ከልብ ወደመነጨ ጸሎት ይቀይሩት። ኢየሱስ ለእርስዎ እና ለሌሎች ያለውን ፍቅር እንዲረዱና እንዲታመኑ ጥንካሬ እና መረዳት እንዲሰጥዎ እግዚአብሔርን ይጠይቁ።
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበን BibleProject ን ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡- https://bibleproject.com/Amharic/