የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎችናሙና

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

ቀን {{ቀን}} ከ28

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ርቆ የራሱን መንገድ እንደመረጠና በዚህም ምክንያት እንዴት እንደተሰቃየ ያሳያል። ነገር ግን እግዚአብሔር የሰው ልጆችን መቅረብ ስለሚፈልግ፣ እንዲሁም ደግሞ ከእርሱ መራቅ ምን ያህል እንደሚያም ስለሚያውቅ፣ ሰላም እንዲሰፍን ኢየሱስን ላከ። በኢየሱስ በኩል ነገር ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ዳግም ወደ ምልዓት ይመለሳል።

ያንብቡ፦

ቈላስይስ 1÷19-23

ምልከታዎን ያስፍሩ፡

በዚህ ንባብ መሰረት፣ እግዚአብሔር ማድረግ የፈለገው ምንድን ነው፣ እንዴትስ በኢየሱስ በኩል ፈጸመው?

ኢየሱስ የሰው ልጅ እንደገና በእግዚአብሔር ቅዱስ መገኘት ውስጥ እንዲሆን ለማድረግ የተቀበለውን እና ተቋቁሞ ያለፈውን ስቃይ ያስቡ። የተሰማዎትን የመደነቅና የምስጋና ስሜት ለመግለጽ ምልከታዎ ወደ ጸሎት እንዲያመራ ያድርጉ።

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 11ቀን 13

ስለዚህ እቅድ

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበን BibleProject ን ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡- https://bibleproject.com/Amharic/

ተዛማጅ እቅዶች