BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎችናሙና
ሐዋሪያው ጳውሎስ ኢየሱስ ራሱ ሰላማችን ነው ይላል። ኢየሱስ የሰውን ልጅ እርስ በእርስ እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር የሚለየውን ነገር በሙሉ አስወግዶ፣ ሰላሙን ለሌሎች ስጦታ አድርጎ አቀርቧል። የኢየሱስ ተከታዮች ይህን የሰላም ስጦታ ለመቀበል፣ ለመጠበቅና ለማስፋፋት የተጠሩ ሲሆን፣ ይህን ማድረግ ትህትና፣ ገርነት፣ ትዕግስት እና ፍቅር ይጠይቃል።
ያንብቡ፦
ኤፌሶን 2÷11-15፣ ኤፌሶን 4÷1-3፣ ኤፌሶን 4÷29-32
ምልከታዎን ያስፍሩ፡
በዚህ ክፍል መሰረት፣ ኢየሱስ በጥል ላይ ያሉ ሁለት ህብረተሰቦች (አይሁድ እና አህዛብ) መካከል ሰላም እንዴት አወረደ? ለምንስ ይህን አደረገ (2÷16ን ይመልከቱ)?
በህይወትዎ ውስጥ ከሆነ ሰው እንደተገለሉ ይሰማዎታል? ከዚህ ሰው ጋር ሰላምን ማጣጣም ይፈልጋሉ? ለምን ይህን ይፈልጋሉ ወይም ለምን አይፈልጉም? ኢየሱስ ሰላም እንዲሰፍን ምን እንዳደረገ ያስቡ። ይህን ሲያሰላስሉ ምን አይነት ጥያቄዎች ወይም ስሜቶች ተፈጠረብዎት?
ኤፌሶን 4÷1-3ን በጥንቃቄ ይከልሱ። ትህትና፣ ገርነት፣ ትዕግስት እና ፍቅር ኢየሱስ ለተከታዮቹ የሰጠውን አንድነት ለማስጠበቅ እንዴት የሚጠቅሙ ይመስልዎታል? ከእነዚህ መንፈሳዊ እሴቶች አንዱ ቢጎድል ውጤቱ ምን ይሆናል? የሌሎችን ምርጫ መጋፋት አይችሉም፣ ነገር ግን ሰላም እንዲሰፍን ዛሬ እርስዎ ሊያደርጉ የሚችሉት አንድ ተግባራዊ ውሳኔ ምንድን ነው?
ኤፌሶን 4÷29-32ን በጥንቃቄ ይከልሱ። ኢየሱስ ይቅር ያለዎት እንዴት ነው? የእርሶን ይቅርታ ማን ይፈልጋል?
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበን BibleProject ን ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡- https://bibleproject.com/Amharic/