BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎችናሙና
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ተስፋ ነገ ከዛሬ ይሻላል ብሎ ለማመን መሰረቱ የእግዚአብሔር ባሕርይ ነው። አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ባሕርይ በአወቀበት መጠን ተስፋው እየጨመረ ይመጣል።
ያንብቡ፦
መዝሙር 130÷1-8
ምልከታዎን ያስፍሩ፡
መዝሙረኛው ስለ እግዚአብሔር ባሕሪይ ምን ይላል?
ስለ እግዚአብሔር ባህሪይ እርስዎ ምን ይላሉ?
መዝሙረኛው እግዚአብሔር ለእስራኤል ምን እንደሚያደርግ ያምናል?
እግዚአብሔር ለእርስዎና ለህብረተሰብዎ ምን እንደሚያደርግ ያምናሉ?
በዚህ ሳምንት የእግዚአብሔር ይቅር ባይ ፍቅር በህይወትዎና በህብረተሰብዎ መካከል እንዴት ሲሰራ ማየት ይፈልጋሉ? 1. መልስዎን ወደ ጸሎት በመቀየር አሁን ለእግዚአብሔር ይንገሩት። እርሱ እየሰማ ነው።
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበን BibleProject ን ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡- https://bibleproject.com/Amharic/