BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎችናሙና

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

ቀን {{ቀን}} ከ28

ተስፈኝነት ሁኔታዎች ተስተካክለው ለበጎ የሚሆኑበትን መንገድ ለማየት መምረጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ተስፋ ግን በሁኔታዎች የተመረኮዘ አይደለም። እንደውም፣ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ተስፋ ያላቸው ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ነገሮች እንደሚስተካከሉ የሚያመለክት ምንም ማስረጃ የሌለባቸውን ከባባድ ወቅቶች ያሳልፋሉ፤ ይሁን እንጂ አሁንም ተስፋ ለማድረግ ይመርጣሉ። ለምሳሌ፣ የእስራኤል ነቢይ የሆነው ሚክያስ ኢፍትሃዊነትና ክፋት በተስፋፋበት ዘመን ይኖር ነበር፤ ግን ደግሞ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርጎ ነበር።

ያንብቡ፦

ሚክያስ 7÷6-8

ምልከታዎን ያስፍሩ፡

ሚክያስ በቁጥር 6 የሚዘረዝራቸውን አንዳንድ ችግሮችና በቁጥር 7 እና 8 የሚሰጠውን ምላሽ ያስተውሉ። በዚህ ጊዜ በዙሪያዎ ካሉ ችግሮች አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው? የሚክያስ ምላሽ ዛሬ የሚያበረታታዎ ወይም የሚሞግትዎ እንዴት ነው?

ሚክያስ ለእግዚአብሔር የጸለየውን ጸሎት መልሰው ለመጸለይ ጥቂት ጊዜ ይውሰዱ። እግዚአብሔር ይሰማዎታል።

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 2ቀን 4

ስለዚህ እቅድ

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበን BibleProject ን ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡- https://bibleproject.com/Amharic/